አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ የበይነ መረብ ጥቃት ሰለባ መሆኑ ተገለጸ።
ኤጀንሲው የሃገሪቱ ትላልቅ ወታደራዊ ግንኙነቶችን ጨምሮ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎችን የሚከታተልና የመረጃ ደህንነት ስርአቱን የሚቆጣጠር ነው።
የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴርም የኤጀንሲው የኮምፒውተር ስርአት ላይ ጥቃት መድረሱን ገልጿል።
በዚህ ሳቢያም የ200 ሺህ ሺህ ሰዎች የግል መረጃ ለጥቃት መጋለጡ ነው የተገለጸው።
ለጥቃት ተጋልጠዋል የተባሉት መረጃዎች፥ ስሞችን እና የማህበራዊ ደህንነት ቁጥሮችን ያካተቱ መሆናቸውም ተገልጿል።
ኤጀንሲው ለወታደራዊ የመረጃ መረብ ደህንነት እንዲሁም በውጊያ ቀጠናዎች ውስጥ የግንኙነት መረቦችን የመከታተልና የመቆጣጠር ሃላፊነትም አለበት።
ከጥቃቱ በኋላም ኤጀንሲው ምርመራ ማድረጉን እና ችግሩን ለማስተካከልና ተጨማሪ ጥቃቶችን ለመከላከል እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
ተፈጽሟል የተባለው የበይነ መረብ ጥቃት ዝርዝር ጉዳይ ባይገለጽም ኤጀንሲው ግን ስጋት ላይ መሆኑ ነው የተነገረው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision