Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት በሱዳን ድንበር በኩል ከሌሎች ፅንፈኛ ሃይሎች ጋር ትስስር በመፍጠር ያደረገውን እንቅስቃሴ ማምከን ተችሏል – ጄነራል ጌታቸው ጉዲና

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሱዳን ድንበር በኩል ከፅንፈኛ ሃይሎች ጋር ትስስር በመፍጠርና ያደረገውን እንቅስቃሴ ማምከን መቻሉን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገለፁ።
የሽብር ቡድኑ በግንባር እያደረገ ያለውን ጥቃት ለማፋጠን ከሱዳን ድንበርና ከሌሎች ፅንፈኛ ሃይሎች ጋር ያደረገው ትስስር የምእራብና የማእከላዊ ጎንደር ብሎም የወልቃይት አካባቢ መስተዳድርና የፀጥታ ሃይሎች ከሰራዊታችን ጋር ጥምረት በመፍጠር ባደረጉት ወደር የሌለው ተጋድሎ ማምከን መቻሉን ጀነራሉ ገልፀዋል ። ለአካባቢው አመራርና ህዝብም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የሽብር ቡድኑ እንኳን ለሌላ ህዝብ ፣ ወጥቼበታለሁ ለሚለው ማህበረሰብ የማይበጅ እንደሆነ የገለፁት ጄነራል ጌታቸው ጉዲና፥ ቡድኑ በህይወት እስካለ ድረስ ከጥፋት የማይመለስና ለእኩይ አላማ የተፈጠረ በመሆኑ ይህን የጥፋት ሀይል ላይመለስ እስከወዲያኛው ማሰናበት ተገቢ እንደሆነም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
እስካሁን የተሰሩ ስራዎች በውጤታማነት የተቋጩት ጠንካራ የትብብርና የመደጋገፍ ባህል በመስፈኑ እንደሆነ የገለፁት ጄነራል መኮንኑ ፥ ከድል ማግስት ያሉ የትንሽነት አባዜዎችን በማኮስመን ትብብራችንን በደነደነ መሰረት ላይ ማስቀመጥ ይጠበቅብናል ብለዋል።
እንደ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገለጻ፥ እንደ ሃገር ትልቆች በመሆናችን እይታችንና ተግባራችን በትልልቅ አጀንዳዎች ላይ ማድረግም እንደሚገባ መናገራቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version