Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የደህንነት አማካሪ ቱት ጋትሉክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤የካቲት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ኔቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የደህንነት አማካሪ ቱት ጋትሉክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በወቅቱም አምባሳደር ነቢል በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለአማካሪው ገለጻ አድርገዋል፡፡

ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ውይይት ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጅት እደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሊደረግ የታቀደው ይህ ሀገራዊ ውይይትም በኢትዮጵያ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች መንግስት ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል ነው ያሉት በዚሁ ወቅት።

መንግስት ለዘላቂ ሰላም ጥረት ቢያደርግም ህወሓት በአጎራባች ክልሎች እያደረሰ ያለውን ጥፋት መቀጠሉን አምባሳደሩ አብራርተዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት የደህንነት አማካሪ ቱት ጋትሉክ በበኩላቸዉ፥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በቅርቡ ያደረጉትን ጉብኝት በማስታወስ በሁለቱ ሀገራት ድንበሮች ላይ ያለዉ የፀጥታ ስራ እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት እንዳለቸዉ የገለፁት አማካሪዉ ሰላምን ለማስፈን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እያሳዩት ያለዉን በሳል አመራር ማድነቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version