አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲክ ቶክ አዲስ የደህንነት መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ ነው።
ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነው ቲክ ቶክ ወላጆች ልጆቻቸው የሚጠቀሙትን የማህበራዊ ትስስር ገጽ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል አዲስ የደህንነት መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ መሆኑን ገልጿል።
መተግበሪያው ወላጆች የማህበራዊ ትስስር ገፅ አድራሻቸውን ከልጆቻቸው ጋር እንዲያገናኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ይህም ወላጆች የልጆቻቸውን የማህበራዊ ትስስር ገጽ አድራሻን በተለያየ መንገድ መቆጣጠርና ልጆቹ የሚመለከቷቸውን ገጾች እንዲከታተሉም ያስችላቸዋል ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈም ልጆች በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚያጠፉትን ጊዜ መገደብ እንደሚያስችላቸውም ተገልጿል።
ይህ መሆኑ ደግሞ ቤተሰብ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ በማድረግ ጤናማ የልጆች አስተዳደግ እንዲኖር እንደሚያስችልም ነው የተነገረው።
ምንጭ፡- news.sky.com/
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision