Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የትምህርት ሚኒስትሩ በሳይንስና ትምህርት ዘርፍ የኢትዮ- ሩሲያን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ላይ ከሀገሪቱ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸውን ትብብር እና የህግ ማዕቀፎች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሀገሪቱ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌት ተረኪን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሳይንስ እና ትምህርት የሁለትዮሽ ትብብር እና የህግ ማዕቀፎቹን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኢትዮጵያ ሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ እየተካሄዱ የሚገኙ የማሻሻያ እቅዶችን በተመለከተ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል።

በሩሲያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን ማሰልጠን የአገራቱ የቆየ ባህል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በኢትዮጵያ ይሠሩ በነበሩ ሩሲያውያን ፕሮፌሰሮች ለኢትዮጵያውያን ይሰጡት የነበረው ሥልጠና ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱም ተጠቁሟል ።

በዚህም የሁለቱ አገራት ህዝቦች እውነተኛ የወዳጅነት ምልክት የሆነው የቀድሞው የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት የአሁኑ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መሆኑም ተመላክቷል።

በኢትዮጵያ ካሉ አንጋፋ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በማብቃት ልሂቅ ማድረጉም ነው የተነሳው።

ለአገራቸውና ለሕዝቦቻቸው የጋራ ተጠቃሚነት ባላቸው ጉዳዮች ላይም በትብብር መስራት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስማማታቸውን በኢትዮጵያ ከየሩሲያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version