የሀገር ውስጥ ዜና

ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ዳያስፖራዎች አሶሳ ከተማ ገቡ

By Meseret Awoke

February 09, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ ሀገር ቤት የመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ዛሬ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገቡ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ አመንቴ ገሺ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ዛሬ ከ60 የሚበልጡ ዳያስፖራዎች አሶሳ ከተማ ገብተዋል።

ከዳስፖራዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ያስታወቁት የቢሮ ሃላፊው÷ የክልሉ ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ገለጻ ይደረግላቸዋል ብለዋል።

የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ በሶስት ቀናት ቆይታቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንደሚጎበኙና የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ስፈራዎችን እንደሚመለከቱ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው የሚታወስ ነው።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!