Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ለሀገሪቱ ሴናተሮች በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ለሀገሪቱ ሴናተሮችና የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል።
አምባሳደሩ በገለፃቸው ወቅት፥ የኢትዮጵያ መንግሥት የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም እና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎችን ከእስር እንዲፈቱ በማድረግ ሰላምን ለማስፈን በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
አሸባሪው ህወሓት በአዲስ መልክ በአፋር እና በአማራ ክልሎች እያደረሰ ባለው ጥቃት የሰላም ጥረቶችን እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን እያደናቀፈ መሆኑንም አንስተዋል።
አምባሳደር ሄኖክ አያይዘውም ፈረንሣይ የኢትዮጵያን የመልሶ ማቋቋም ጥረት እና የታቀደውን ብሔራዊ ምክክር ለመደገፍ እያሳየችው ላለው ዝግጁነት ማመስገናቸውን ፓሪስ ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version