አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ የዲስፕሊን ግድፈት በፈፀሙ 3 ክለቦችላይ የሊጉ የዲስፒሊን ኮሚቴ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ክለቦችም÷ ድሬዳዋ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳና እና ወላይታ ዲቻ ሲሆኑ÷ ደጋፊዎቻቸው በሜዳ ውስጥ ባሳዩት ያልተገባ ድርጊት ነው የቅጣት ውሳኔ ሊተላለፍባቸው የቻለው፡፡
ሀዲያ ሆሳና በጅማ አባ ጅፋር 4 ለ 2 በተሸነፈበት ጨዋታ እንዲሁም ወላይታ ዲቻ ከአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው ጨዋታ ደጋፊዎቻቸው የዕለቱን ዋና ዳኞች አስፀያፊ ስድብ መሳደባቸውን የሊጉ የዲስፒሊን ኮሚቴ በቀረበለት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
ክለቦቹ በ11ኛው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ያሳዩትን የዲስፕሊን ግድፈት ተከትሎም በእያንዳንዳቸው የ75 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል፡፡
በተመሳሳይ የድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸማቸው የሊጉ ዲስፒሊን ኮሜቴ ክለቡ በ50 ሺህ ብር እንዲቀጣ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!