የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በ35ኛው የህብረቱ ጉባኤ ላይ የታደሙ የተለያዩ መሪዎች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 07, 2022

አዲስ አበባ፣ጥር 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ ታድመው ከነበሩ የተለያዩ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የጅቡቲውን ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና የኮትዲቯሩን ፕሬዚዳንት ኦላሳን ኦታራን አነጋግረዋል።