Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በ35ኛው የህብረቱ ጉባኤ ላይ የታደሙ የተለያዩ መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ጥር 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ ታድመው ከነበሩ የተለያዩ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የጅቡቲውን ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና የኮትዲቯሩን ፕሬዚዳንት ኦላሳን ኦታራን አነጋግረዋል።

ከመሪዎቹ ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይት የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተመለከተ እና ቀጠናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ነው ውይይት ያደረጉት።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ከቻድ እና አልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋርም በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ የሚመራ የሴቶች የልኡካን ቡድንንም አነጋግረዋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነዉ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version