የሀገር ውስጥ ዜና

35ኛው የኅብረቱ ጉባኤ በሰላምና በስኬት ተጠናቆ መሪዎች ወደየሀገራቸው እየተመለሱ ነው

By Feven Bishaw

February 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት በመጠናቀቁ የጉባኤው ተሳታፊ መሪዎች ወደ የሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው፡፡

በዚህም መሰረት እስካሁን ባለው መረጃ  የኬንያ ፣የሞሪታኒያ፣የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኮሞሮስ ፣ ጋና፣ ቤኒን፣ ዛምቢያ፤ ኮትዲቯር፥ ሊቢያ፣ ጅቡቲ፣ ሲሸልሽ ፣የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የኒጀር ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም  የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላት ወደየሀገራቸው ተመልሰዋል።