የሀገር ውስጥ ዜና

ሕብረቱ አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ በምታገኝበት ሁኔታ ላይ መከረ

By Feven Bishaw

February 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ም/ቤት ለአፍሪካ የውሳኔ ሰጪነት ቦታን መስጠት የሚያስችለው ሪፎርም እንዲያደርግ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አፅንኦት ሰጥቶ መምከሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

አምባሳደር ዲና ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አፍሪካ በዓለም አቀፉ መድረክ ከውሳኔ ሰጪዎች አንዷ መሆኗ የግድ እውን ሊሆን እንደሚገባ መስማማታቸውን ገልጸዋል።