የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ከህመማቸው ፈጥነው እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገለፁ

By Feven Bishaw

February 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ከህመማቸው ፈጥነው እንዲያገግሙና ለጤንነታቸው መልካም ምኞታቸውን ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ÷ፕሬዝዳንት ኤርዶኻንና ባለቤታቸው በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ለፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን እና ቀዳማዊት እመቤት ኢሚኒ ኤርዶኻን ፈጣን ማገገምንና ጤንነትን እመኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡