የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎችን አመሠገኑ

By Mekoya Hailemariam

February 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎችን አመሠገኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወዳጅነት አደባባይ ለአፍሪካ መሪዎች የዕራት ግብዣ መርሐ ግብር አዘጋጅተዋል።

ማምሻውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በጉባኤው ላይ የተገኛችሁትን ሁሉ አመሰግናችኋለሁ” ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ሁሌም እጆቿን ዘርግታ ትቀበላችኋለች” ነው ያሉት በመልዕክታቸው።