የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለቸው የህብረቱ ጉባኤ ጫናዎችን ተቋቁማ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ መሆኗን ያሳየ ነው – የውጭ ሃገራት የሚዲያ ባለሙያዎች

By Meseret Awoke

February 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለችው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጫናዎችን ተቋቁማ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ መሆኗን ያሳየ መሆኑን የውጭ ሃገራት የሚዲያ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ባለሙያዎቹ ጉባኤው የአዲስ አበባን ብሎም የኢትዮጽያን መረጋጋትና አንድነት ያሳየ እንደሆነ አብራርተዋል ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ህብረትን ለመዘገብ የመጣው እና የአፍሪካ 24 ሚዲያ ላይ በግሉ የሚጽፈው ጋዜጠኛ አህመድ ኢብራሂም ፥ ኢትዮጵያ ጫናዎችን ተቋቁማ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን እያስተናገደች መሆኑ የዲፕሎማሲው መስክ ስኬት ተደርጎ ይወሰዳል ብሏል ፡፡

ከኮንጎ የመጡት የሚዲያ ባለሙያ ዝንፒዮ ወፍናው፥ ኢትዮጵያ የቆመችበትን ሃቅ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስረዳት በዲፕሎማሲው መስክ ያከናወነቻቸው ስራዎች ውጤት በማምጣታቸው ነው ይላሉ ፡፡

በተለይም የበቃ እንቅስቃሴ ራእይ ስለ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ጣልቃ ገብነትን ስላለመቀበል እንዲሁም ስለ ሃገር በጋራ መቆም በመሆኑ ኢትዮጵያ ሌሎች ሃገራትን ያነቃቃችበት እንደሆነም ባለሙያዎቹ አብራረተዋል ፡፡

ከማላዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጡት ናንሴ ቴምቦ ፥ አፍሪካውያን ካለፉ ስህተቶች ተምረው ቀና የሚሉበት ጊዜ መሆኑን አንስተው፥ በትብብር ችግሮቻቸውን ለመፍታት በርትተው መስራት አለባቸውም ነው ያሉት ፡፡

በአወል አበራ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!