የሀገር ውስጥ ዜና

የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

February 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ በ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!