Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል፡፡
 
ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሶማሊያ፣ የዚምባብዌ፣ ዛምቢያ፣ የሞሪታንያ፣ የኒጀር እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንቶች፥ የኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የቻድና የጋቦን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ናቸው በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የገቡት፡፡
 
በዚሁም መሰረት የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ፣ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ፣ የሞሪታንያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ኡልድ ኤል-ጋዝዋኒ፣ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማም፣ የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ምባንጎ፣ የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር አልበርት ፓሂሚ ፓዳኬ እና የጋቦን ጠቅላይ ሚኒስትር ሮስ ክሪስቲያን ኦሱካ ራፖንዳ በሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡ መሪዎች ናቸው።
 
በተጨማሪም የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፎውስቲን አርቸንጅ፣ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄሲካ አሉፖ፣ የኒጀሩ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ባዙም፣ የሊቢያው ፕሬዚዳንት መሃመድ ያውንስ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጉኤሶ ፣ የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁሌስ ማዳ ቢዮ የሳሃራዊ ፣ የአረብ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ጋሊ እና የጋና ፕሬዚደንት ናና አኩፎ አዶ ለጉባኤው አዲስ አበባ ገብተዋል።
 
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፊሊክስ ሺሴኬዲ፣ የብሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሬስት ንዳያሽሜ እና የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒም በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
 
መሪዎቹ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን፣ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፣ የኢንዲስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው።
 
በበርናባስ ተስፋዬ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version