የሀገር ውስጥ ዜና

በተጠቆሙት 42ቱ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ነገ የሕዝብ አስተያየት ይሰጣል

By Feven Bishaw

February 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አግባቦች የተጠቆሙት 42ቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ነገ 8 ሰዓት ከ30 ላይ የሕዝብ አስተያየት እንደሚሰጥባቸው ተጠቆመ፡፡

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ተቀባይና አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ሔኖክ ስዩም÷ በሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኩ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ አካላት ፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ፣ የክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሲቪክ ማሕበራት ተወካዮች እንደሚገኙ ገልፀዋል ።