አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ዛሬ ምሽት የሚደረገውን የግብፅ እና ካሜሮን ጨዋታ አስመልከቶ አንጋፋው እግር ኳስ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ አስተያይቱን ሰጥቷል፡፡
ካሜሮናዊው የቀድሞው የባርሴሎና አጥቂ ሳሙኤል ኤቶ ቀደም ሲል በሰጠው አስተያየት፥ አሁን ላይ ሁላችንም ስለ አንድ ጉዳይ ብቻ ነው ምናስበው እሱም የዛሬ ምሽቱ ፍልሚያ ነው ብሏል።
የካሜሮን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች እስካሁን ያደረጋችሁትን የድል ጉዞ በዛሬው ጨዋታ መድገም አለባችሁ፣ ጨዋታው ከጦርነት አያንስም፣ጦርነቱን ለማሸነፍ ሁላችሁም ተዘጋጁ ሲል ኤቶ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
የግብፅ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ካርሎስ ኬሮዥ የቀድሞው የባርሴሎና አጥቂ ሳሙኤል ኤቶ የሰጠውን አስተያይት ተችተዋል፡፡
በጣም አሳዛኝ አስተያየት እና በጣም መጥፎ አገላለፅ ነው፣ ለካሜሮናውያን መጥፎ መልዕክት አስተላልፏል ብለዋል፡፡
ሳሙኤል ኤቶ ከጨዋታ በፊት የጦርነት ነጋሪት መጎሰሙ በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ውስጥ በነበረበት ወቅት ምንም ነገር እንዳልተማረ ማሳያ ነው ሲሉ የ68 አመቱ ፖርቹጋላዊ አስልጣኝ የኤቶን አስተያይት አጣጥለውታል።
አስልጣኙ በተጨማሪም አሰልጣኝ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በኢቶ ላይ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁ ሲሆን ፥ የሰጠውን ሀሳብም እንዲያስተካክል ማሳሰባቸውን ስፖርት ስታር ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!