Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጡን መፋለም አስፈላጊ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጡን መፋለም አስፈላጊ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳን ያካተተ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ቡድን በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በድርቅ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለመገምገም ጉብኝት አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉትም የአፍሪካ ቀንድ ከከባድ ድርቅ ጋር በሚታገልበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን ያሉት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቸገሩ ማኅበረሰቦችን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጡን መፋለም አስፈላጊ ሲሆን÷ የመካከለኛ ጊዜ የውኃ ልማት ፕሮጀክቶች ደግሞ ችግሮች ሳይከሠቱ መፍትሔ ለማበጀት ያስችላሉ ነው ያሉት።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version