Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ 3ሺህ የሚጠጉ ወታደሮቿን ወደ አውሮፓ ልታሰማራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩስያ ዩክሬንን ልትወር ነው በሚል ሰበብ አሜሪካ ወደ 3ሺህ የሚጠጉ ወታደሮቿን ወደ ሶስት የአውሮፓ አገሮች ልታሰማራ መሆኗን አሳወቀች፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በቀጠለው ግጭት ምክንያት በመጪዎቹ ቀናት ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አውሮፓ ( ጀርመን፥ ፖላንድና ሮማንያ) እንደምታሰማራ የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) አስታውቋል።
ሩስያ በቅርቡ ከ100 ሺህ በላይ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷን ተከትሎ ወረራ ልትፈጽም ትችላለች የሚል ስጋት በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በኩል እንደተፈጠረ ዘገባው አውስቷል፡፡
ሩስያ ስጋቱ ትክክል እንዳልሆነ ብትገልጽም ዩክሬን የኔቶ አባል ሀገር እንድትሆን የሚደረገውን የውጭ ሀገራት ግፊት ሩሲያ መቃወሟን ተከትሎ ውጥረቱ መባባሱ ይታወቃል።
አሜሪካ የዩክሬን ደህንነት እስካልተጠበቀ ድረስ ሀገሪቱን ከአደጋ ለመታደግ ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ ፥ ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ጉዳይ ላይ የምታደርገው እንቅስቃሴ ሩሲያን ወደ ጦርነት አስገድዳ ለማስገባት እየሞከረች ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡
ዋሽንግተን ግጭቱን እንደ ምክንያት በመጠቀም በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል እንደ መልካም እድል ለጠቀም ጥረት እያደረገች ነው ሲሉም የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል፡፡
ፑቲን ዩክሬን ወደ ኔቶ አባልነት ልትገባ የምትችልበት ግፊት ለዓለም ሰላም የህልውና ስጋት ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version