የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ እና የጣሊያን አምባሳደር የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

By Alemayehu Geremew

February 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ በጤናው ዘርፍ የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ማካሄዳቸው ተገለጸ፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በጤናው ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር እና በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ላይ በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሯ ጣሊያን በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ያላሰለሰ ሙያዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ እና ጣሊያ ን በጤናው ዘርፍ ያላቸው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ጣሊያን በኮቪድ-19 ላይ የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን በኢትዮጵያ ከጣሊያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡