Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ መካሄዱ የሀገርን ገጽታ እንደ አዲስ ለተቀረው አለም ለመገንባት ልንጠቀምበት ይገባል-ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ መካሄዱ የሀገርን ገጽታ እንደ አዲስ ለተቀረው አለም ለመገንባት ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ።
ከፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው በድሬድዋ ዩኒቨርሰቲ የፖለቲካና የአለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሱራፌክ ጌታሁን በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ላይ ጥርጣሬ ለነበራቸው ወገኖች የመሪዎቹ ስብሰባ በመዲናዋ መካሄድ ምላሽ የሚሰጣቸው ይሆናል ነው ያሉት ።
የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት በማሳያትም አዲስ ገጽታን ለመገንባት እድል ይሰጣል ብለዋል ።
በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የአለም አቀፍ ህግ መምህር አቶ ሀይሉ ነጋ ፥ባለፉት ጊዜያት በርካታ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ስም በማጠልሸት ላይ ማተኮራቸውን ያስታውሳሉ።
ከቀናት በሃላ የሚካሄደው የመሪዎቹ ጉባኤም ይህን ገጽታ ለመቀየር ጉልህ ሚናን የሚጫወትና ሰላማችንን ለተቀረው አለም የምናሳይበት አጋጣሚ ነው ብለውታል።
ምሁራኑ በጉባኤው አማራጭ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ጭምር በመጠቀም ገጽታን ማሻሻል ስራዎች ላይ መሰራት አለበት ብለዋል።
በሀይለየሱስ መኮንን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version