Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በተለያዩ ከተሞች ለውጡን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማ ለውጡን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
 
በሰልፉ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ በከተማውና አካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፍዋል።
 
ነዋሪዎቹ በሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እያመጡት ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴና የሀገር አንድነት የሚያበረታቱ መፈክሮችን በማንገብ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
 
የመደመር አስተሳስብና የብልጽግና ጉዞውን ለማስቀጠል የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
 
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል በበደሌ ዞን፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች ነዋሪዎች ለውጡን በመደገፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

እንዲሁም በአፋር ክልል በሀንሩካ ወረዳ፣ በያሎ ወረዳ፣ አዋሽ ፈንቲአሌ ወረዳ፣ ጎሊና ወረዳ፣ በአርጎባ ልዩ ወረዳና በአዋሽ ሱባህ ኪሎ ከተማ የተጀመረውን ለውጥ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

በተሾመ ሃይሉ
 
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision
Exit mobile version