Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአገልጋይነትን መንፈስ ተላብሶ አገራዊ ኃላፊነትን በአግባቡ የሚወጣ አመራር ማብቃት ያስፈልጋል – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአገልጋይነትን መንፈስ ተላብሶ አገራዊ ኃላፊነትን በአግባቡ የሚወጣ አመራር እየገነቡ ማብቃት እንደሚያስፈልግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።

የየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” ርዕስ ዙሪያ የአመራር ግንባታ የውይይት መድረክ በአሶሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር ተገኝተዋል።

ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም በተገኙበት ለመድረኩ በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገራዊውና የክልሉ የፖለቲካና የአስተዳደር ታሪክ የራሱን ቀለምና ቅርጽ ይዘት በሚመለከት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳር አቶ ጌታሁን አብዲሳ አጭር ኦሬንቴሽን ሰጥተዋል፡፡

ብልፅግና በምርጫ ያገኘው ድልን ሳይሆን ህዝብ የማገልገል ዕድልን ጭምር ነው ያሉት ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር ናቸው፡፡

ይህን ኃላፊነት ለመወጣት የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ አገራዊ ኃላፊነትን በአግባቡ የሚወጣ አመራር ማብቃት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የአመራር፣ የተግባር ጥንካሬና የፓርቲ ስነ ምግባርን ከፍ በማድረግ የእያንዳንዱ አመራር ጥንካሬ እየጎለበተ፥ ድክመቱ የሚታረምበት መድረክ እንደሚሆንም አቶ ኢስሃቅ መግለጻቸውን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version