አዲስ አበባ፣ጥር 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ መንግስት መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለጹ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እያካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል::
የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ወ/ሮ ትዕግስት ይልማ፥ ለአባላትና ለተጋባዥ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል::
የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት መገናኛ ብዙሃን ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል::
የሚዲያ ባለሙያዎች ዋነኛ ስራቸውን ቸል በማለት ፖለቲከኛና ማህበራዊ አንቂ በመሆን ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፥ የተሻለው ግን በያዙት ሚዲያ የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆኖ ማገልገል ነው ብለዋል::
ሚዲያ የተለየ ህዝባዊ ወገንተኝነትና አገልግሎት የሚጠበቅበት እንደመሆኑ፥ ሲቋቋምም ሆነ ሲሰራ በዚሁ እሳቤ ሊሆን ይገባዋል ነው ያሉት አቶ መሀመድ::
በኢትዮጽያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ተወካይ ክላውድ ብሌቪን በበኩላቸው፥ ሀገራቸው ለሚዲያው ዕድገት ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ ገልፀዋል::
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት 46 የሚዲያ ተቋማትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፥ 16 የአዳዲስ አባላትን ጥያቄ ተቀብሎ አጽድቋል::
በሸለመ ከቤ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!