የሀገር ውስጥ ዜና

የጂቡቲ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፣ ሊቢያና ሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

By Mekoya Hailemariam

February 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፣ ሊቢያና ሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ።

በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የጂቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሀሙድ አሊ የሱፍ፣ የሊቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናጅላ አልማንጉሽ እና የሞሪታኒያ አረባዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስማኤል ኡልድ ሼክ አህመድ ለሊት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ማለዳ ላይም የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ናለዲ ፓንዶር እና የሴኔጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሲታ ቶል ሳል አዲሰ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ሹም አምባሳደር ምህረተዓብ ሙሉጌታ እና የፕሮቶኮል ጉዳዮች ሹም በሆኑት አምባሳደር ፈይሰል አሊይ አቀባበል እንደተደረገለት ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።