የሀገር ውስጥ ዜና

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

January 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የወደመው የወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መልሶ ለማስጀመር የሚረዳ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት የቤተ ሙከራ እቃዎች፣ ኮምፒውተሮች ፣ጠረጴዛዎች፣ አልጋዎች፣ ፍራሾች እና የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ነው ድጋፍ ያደረገው።