አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጀርመን በተፈጸሙ ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች ዘጠኝ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ።
ጥቃቶቹ በምዕራባዊ የሃገሪቱ ክፍል ሃናኡ በምትባል ከተማ በታጣቂ የተፈጸመ መሆኑን ፖሊስ አስታወቋል።
በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው።
ጥቃቱን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ማንነቱ ካልተገለጸ ግለሰብ ጋር ህይዎቱ አልፎ መገኘቱንም ነው ፖሊስ የገለጸው።
ግለሰቡ ጥቃቱን ያደረሰበት ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን ፖሊስም ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision