Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ኪልበቲ ረሱ በህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ የፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ በህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰልፍ በኤሊደአር ወረዳ ሀዩ ከተማ ተካሄደ።
የሀዩ ከተማ ነዋሪዎች “ጁንታው በህጻናት፥ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ የፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ግድያ በጽኑ እናወግዛለን” በሚል መሪ ቃል ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ሴቶችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ሰልፈኞቹ “ጁንታው በህጻናት ሴቶች እና አዛውንቶች ላይ የፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ተግባር በጽኑ እናወግዛለን፣ጁንታው በንጹሀን ላይ እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባር በፍጥነት ሊያቆም ይገባል፣ አሸባሪው ህወሓት ታሪካዊ የአፋር ህዝብ ጠላት ነው” የሚሉና የተለያዩ መልእክቶችን በሰልፉ ላይ አሰምተዋል።
አሸበሪው ህወሓት በኪልበቲ ረሱ (ዞን) የተለያዩ ወረዳዎች ከ150 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ አፋር ክልል ዘልቆ በመግባት ንፁሃን አርብቶ አደሮችን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ አሰቃቂ እና እጅግ ዘግናኝ የሆነ የዘር ማጥፈት እልቂት መፈጸሙን ከክልሉ መንግስት ኮሙኑኬሽን ያገኘነው መረጃ መላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version