Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በ1500 ሜትር በማንሃተን ከተማ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በኒዮርክ ማንሃተን በተካሄደው የሴቶች የ1500 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በውድድሩ አክሱማዊት አምባየ 1ኛ፣ ሂሩት መሸሻ 2ኛ እና ፍሬወይኒ ሃይሉ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቀዋል፡፡

በፈረንጆች 2022 እየተካሄደ ያለው ይህ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ዛሬም ሌሎች ውድድሮችን በማካሄድ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version