Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩኒሴፍ የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ረገድ ድጋፍ ስለሚያደርግባቸው ሁኔታዎች ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና ተያያዥ የዘርፉ ተግባራትን ለመደገፍ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ምክክር አካሄዷል።
በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ሚካኤል ሴርቫዲ ጋር ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ቀንን በማስመልከት መወያየታቸው ተመልክቷል።
በውይይታቸውም ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የመምህራን የሙያ ብቃትን ለማሳደግ፣ በትምህርት ተደራሽነትና ካሪኩለም ለውጥ እንዲሁም በትምህርት አሰጣጥ ጥራት ላይ ድጋፍ ስለሚያደርግበት ሁኔታ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version