የሀገር ውስጥ ዜና

ድርቅን በዘላቂነት ለመከላከል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

By Meseret Awoke

January 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን ነው ያሉት።

ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የተጀመሩ የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እንደሚፋጠኑም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!