ስፓርት

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ተጀመረ

By Meseret Awoke

January 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው 11ኛው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ራስ ሐይሉ ጅምናዚየም ዛሬ ተጀምሯል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና እስከ ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ይቆያል።

በሻምፒዮናው ላይ በወንዶች አዘጋጇ ኢትዮጵያን ጨምሮ አልጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም በሴቶች ደግሞ ኢትዮጵያ፣ አልጀሪያና ደቡብ አፍሪካ ይሳተፋሉ።

ሻምፒዮናው በዓለም አቀፍ ደረጃ በዱባይ አዘጋጀነት ለሚካሄደው የዓለም ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር አፍሪካን የሚወክሉ አገራት የሚለዩበት እንደሆነም ተገልጿል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!