አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 25 ሺህ ሯጮች የሚሳተፉበት 21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመዲናችን በደማቅ ሁኔታተካሄደ።
የ21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ከጎረቤት አገሮች የመጡ አትሌቶች እና የሩጫው ተሳታፊዎች ተገኝተዋዋል።
በተካሄደው የአትሌቶች ሩጫ በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው 1ኛ ስትወጣ ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር 2ኛ ፣መልክናት ውዱ 3ኛ ውድድሯን አጠናቃለች።
በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ 1ኛ ሲወጣ ፣አትሌት ጌታነህ ሞላ 2ኛ፣ አትሌት ቦኪ ድሪባ 3ኛ ደረጃን አግኝቷል።
ሩጫው እየተካሄደ ያለው “መጸዳዳት በሽንት ቤት” በሚል መሪ ቃል ነው።
ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረውን የ2014 ቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።
ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ በተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፥ ላለፉት 20 ዓመታት ሲካሄድ የቆየ እና በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የስፖርት ፌስቲቫል መሆኑ ይታወቃል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ፥ በዓለም በ6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሲሆን፥ ከኢትዮጵያውን ባሻገር ከተለያዩ ዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎችም የሚሳተፉበት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 21ኛውን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች የሆነውን ኃይሌን በታላቁ ሩጫ ስናመሰግነው ዝግጅቱ ለአትሌቲክስ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ አኳያ ብቻ ሳይሆን፥ ኢትዮጵያዊ መሰባሰብን፣ ኢትዮጵያዊ ትስስርን፣ ኢትዮጵያዊ መቀራረብን የምንፈጥርበት፤ በብሔር፣ በቋንቋና በሐይማኖት የማንታጠርበት፣ የሁላችን የሆነ ታላቅ ዝግጅትን ስላስጀመረልን ጭምር ነው ብለዋል።
ታላቅ ሩጫ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች፣ ከዚያም በመላዋ አፍሪካ፤ ብሎም በመላው ዓለም የኢትዮጵያን ስም የሚያስጠራ ታላቅ ክንዋኔ ሆኖ እንደሚስፋፋ እምነታቸው መሆኑን አመልክተው፥ ለዚህም መንግሥት አስፈላጊን ድጋፍ ሁሉ ይሰጣል ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!