የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይጀምራሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ መካሄድ ይጀምራሉ፡፡
የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠኝ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ ከተማ የተካሄዱ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅትን ተከትሎ ታህሣሥ 15 መቋረጡ ይታወሳል።
የሊጉ አስተዳዳሪ አካልም በጊዜያዊነት አፍሪካ ዋንጫው ከተጠናቀቀ ከአምስት ቀናት በኋላ ሊጉን ለመቀጠል አቅዶ የነበረ ቢሆንም ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ መሰናበቱን ተከትሎ የሊጉን የመጀመሪያ ቀን አጢኖ ውሳኔ አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ምሽት ከካሜሩን ተነስቶ አዲስ አበባ መግባቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ክለቦች ሰባት የልምምድ ቀናት በመስጠት ጥር 20 (ቀጣይ አርብ) ሊጉ በድሬዳዋ እንዲቀጥል መወሰኑን ከሊጉ አስተዳዳሪ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!