አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኢትዮጵያ የምታስገባው የቡና ምርት መጠን በ196 በመቶ አደገ።
በትናንትናው እለት በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የተሳተፉበት ሰሚናር ተካሂዷል።
ሰሚናሩ በዋናነት ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም ውሳኔዎች አፈፃፀምን መከታተል ዓላማ ያደረገ ነበር።
በዚህ ሁነት ላይ ብቻ በአምስት ሰከንድ ውስጥ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ቡና እሽጎች መሸጣቸውን ነው በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ዉ ፔንግ ያስታወቁት።
በፈረንጆቹ 2021 ዓመተ ምህረት ላይ ቻይና ከኢትዮጵያ ያስገባቸው የቡና ምርት መጠን ከቀደመው ዓመት በ196 በመቶ ማደጉን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በሚቀጥሉት ዓመታት ቻይና መጠኑ ከፍ ያለ የግብርና ምርት ከአፍሪካ ሀገራት ታስገባለች ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!