ዓለምአቀፋዊ ዜና

ብሪታኒያ ዝቅተኛ የሙያ ክህሎት ላላቸው ሰራተኞች ቪዛ እንደማትሰጥ ገለጸች

By Tibebu Kebede

February 19, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታኒያ ዝቅተኛ የሙያ ክህሎት ላላቸው ሰራተኞች ቪዛ እንደማትሰጥ አስታወቀች።

ከአውሮፓ ህብረት ጋር ከፈጸመችው ፍቺ በኋላ መንግስት አዲሱን የስደተኞች እቅድ ይፋ አድርጓል።

በዚህም የብሪታኒያ መንግስት አሰሪዎች በዝቅተኛ የሰራተኛ ዋጋ ላይ ያላቸውን እምነት በመተው የሰራተኞችን አቅም ማሳደግ እና አውቶሜሽን ቴክኖሎጂን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።

የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት በፈረንጆቹ 2020 ህዳር ወር መጨረሻ ከተጠናቀቀ በኋላም አውሮፓውያንም ሆኑ የሌላ ሀገር ዜጎች ከብሪታኒያውያን ጋር እኩል እንደምታስተናግድ ሀገሪቱ አስታውቃለች።

ሆኖም የሌበር ፓርቲ ምቹ ባልሆነ አካባቢ ሰራተኞችን መሳብ ከባድ መሆኑን ነው ያስታወቀው።

የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ፕሪቲ ፓቴል አዲሱ ስርዓት ወደ ብሪታኒያ ለሚመጡ ዜጎች መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል።

እቅዱ የስደተኞችን ቁጥር ከመቀነስ ባለፈ ውጤት ተኮር የስደተኞች ስርዓትን ለመተግበር ይረዳል ተብሏል።

በዚህ አሰራር መሰረት ከውጭ ሀገራት ወደ ብሪታኒያ የሚገቡ ሰራተኞች እንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር እና ተገቢ የሆነ የስራ ክህሎት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመላክቷል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!https://t.me/fanatelevision