ቢዝነስ

አየር መንገዱ ለጥምቀት በዓል ወደ ጎንደር የሚሄዱ ሰዎችን ለማጓጓዝ በአንድ ቀን ብቻ 22 በረራዎችን አደረገ

By Feven Bishaw

January 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ ጎንደር የሚሄዱ መንገደኞችን ለማጓጓዝ በአንድ ቀን ብቻ 22 በረራዎች ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ይህን ተከትሎ አየር መንገዱ ባስተላለፈው መልዕክት “ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለጥምቀት በዓል አከባበር ለሚጓዙ ደንበኞቻችን በቀን 22 በረራዎች በማድረጋችን ደስታ ይሰማናል ብሏል” ።

የጥምቀት በዓል በልዩ ሁኔታ ደምቆ ከሚከበርባቸው አካባቢዎች መካከል የጎንደር ከተማ ዋነኛው ናት።

ዘንድሮም በከተማዋ ጥምቀትን በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። በተለይም የወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተቀብለው የመጡ ዳያስፖራዎች በዓሉን በከተማዋ ለማክበር በስፋት በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።