የሀገር ውስጥ ዜና

ከውጪ የሚገቡ የግንባታ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ለማስቀረት እንሠራለን – ኢንጅነር ታከለ ኡማ

By Alemayehu Geremew

January 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የተመራው ቡድን በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለውን ሴራሚክ ፋብሪካ ጎበኘ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ በቢሾፍቱ የተገነባው ኢንዱስትሪ በቀጣይ ከውጪ የሚገቡ የግንባታ ግብአቶችን ለማስቀረትና ሀገራዊ በሆኑ ምርቶች አቅማችንንና ሀገራዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት ያስችለናል ብለዋል፡፡

በቀጣይም የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ዘርፍ የማዕድን አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲበራከቱ እንሰራለንም ብለዋል፡፡

ሥራ ላይ ያሉ አብዛኛዎቹ የማዕድን ኢንዱስትሪዎችም ያሉባቸውን የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግሮች ቀርፈን በሀገር ውስጥ ግብአት ለመተካት ሀገራዊ አቅማችንን በተቀናጀ መልኩ እንጠቀማለንም ነው ያሉት፡፡

የሴራሚክ ፋብሪካ ግንባታም ተጠናቆ ወደ ምርት እንዲገባ ከኦሮሚያ ክልል ባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት ሠርተን ውጤቱን በጥቂት ወራት ውስጥ እናያለን ማለታቸውን ከማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡