Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባፉሳም ከተማ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካሜሮኗ ባፉሳም ከተማ መግባቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ።
ዋልያዎቹ ያለፉትን ሀያ ቀናት የቆዩበት ያውንዴ ከተማን በመልቀቅ የምድቡን ሶስተኛ ጨዋታ የሚያከናውኑበት ባፉሳም ከተማ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 9:10 ላይ ደርሰዋል።
የቡድኑ አባላት በስፍራው ሲደርሱ የባፋሳም ከተማ ከንቲባ እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
ብሄራዊ ቡድናችን በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን ቆይታ በታጊዶ ሪዞርት የሚያደርግ ይሆናል ሲል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version