በቀጣዩ አመት የሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሰኔ እስከ ሀምሌ ባሉት ጊዜያት እንደሚካሄድ ካፍ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሰኔ 23 እስከ ሀምሌ 23 2023 ድረስ እንደሚካሄድ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌድሬሽን/ካፍ አስታውቋል።
በቀጣይ አመት በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚካሄደው አህጉራዊው ውድድር ከዚህ በፊት ከሚደርግበት የጥር ወር ወደ ሰኔ የተቀየረበት ምክንያት ከሌሎች አቻ ውድድሮች ጋር የመርሃ ግብር መደረራብ እንዳይፈጠር በማሰብ መሆኑን ነው ካፍ የገለፀው።
የአፍሪካ ዋንጫ ከዚህ ቀደም በ2019 በግብፅ አዘጋጅነት በተመሳሳይ ሰኔ ወር ላይ መድረጉ የሚታወስ ነው።
ኮትዲቯር ውድድሩን ለማስተናገድ ሶስት አዳዲስ ስታዲየሞችን እየገነባች ሲሆን፥ ሁለቱን ስታዲየሞች ደግሞ እያደሰች እንደምትገኝ ዘ-ጋርዲያን ስፖርት በዘገባዉ አስታዉቋለ።
ሀገሪቱ የአፍሪካ ዋንጫን ለሁለተኛ ጊዜ የምታስተናግድ ሲሆን ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ1984 ማስተናገዷ የሚታወስ ነው ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
–
Distribution score
Boost post
Like
Comment
Share