አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አወዛጋቢ የዳኝነት ስርዓት በተስተዋለበት የማሊ እና ቱኒዚያ ጨዋታ ቱኒዚያ ያቀረበችውን ይግባኝ ዉድቅ ማድረጉን ካፍ አስታውቋል።
የጨዋታው የመሀል ዳኛ ጃኒ ሲካዝዌ ጨዋታው ከተጀመረ ጀምሮ አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ከመወሰን በተጨማሪ፥ የ90 ደቂቃ መደበኛ ሰዓት ከማለፉ በፊት ጨዋታውን ሁለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ፊሽካቸውን አሰምተዋል፡፡
አወዛጋቢው የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ብቻ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶች የተሰጡ ሲሆን፥ ስምንት የተጨዋች ቅያሬዎችም ተደርገውበታል፡፡
በማሊ የ 1-0 ሽንፈት ያጋጠማት ቱኒዚያ፥ የእለቱ ዳኛ የጨዋታ ጊዜ ሳያልቅ ጨዋታው እንዲቆም ማድረጋቸውን ተከትሎ የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ይግባኝ ጠይቃለች፡፡
ካፍ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የካፍ አዘጋጅ ኮሚቴው የቱኒዚያን ይግባኝ መርምሮ ውድቅ ማድረጉን እና የጨዋታውን ውጤት በማሊ 1-0 አሸናፊነት እንዲጸና ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የካፍ መግለጫ ስለ እለቱ ዳኛ ሁኔታ የጠቀሰው ነገር የለም፡፡
ቱኒዚያ ቀጣዩን ጨዋታ እሁድ ጥር 16 ከሞሪታኒያ ጋር የምታደርግ ሲሆን፥ ማሊ በተመሳሳይ ቀን ከጋምቢያ ጋር ትጫወታለች፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!