Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ 59 ኩንታል ካናቢስ አደንዛዥ እጽ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ 59 ኩንታል የካናቢስ አደንዛዥ እጽ ተያዘ።

የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ሃላፊ ኮማንደር አዳሙ አባተ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በዱግዳ ዳዋ ወረዳ 59 ኩንታል የካናቢስ አደንዛዥ እጽ በዛሬው ዕለት ተይዟል።

አደንዛዥ እጹ በአንድ የጭነት ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ተጭኖ ከሻሸመኔ ወደ ሞያሌ በመጓዝ ላይ እያለ ነው በህዝብ ጥቆማ የተያዘው።

በወሩ ለሁለተኛ ጊዜ መሰል አደንዛዥ እጽ መያዙን የገለጹት ኮማንደር አዳሙ፥ በአካባቢው የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በማርታ ጌታቸው

Exit mobile version