የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌ እና በማረቆ ወረዳ ማህበረሰብ መካከል የእርቅ ስነ ስርዓት እየተካሔደ ነው

By Meseret Awoke

January 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌ እና በማረቆ ወረዳ ማህበረሰብ መካከል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በሁለቱም ወገን የሀገር ሽማግሌዎች የእርቅ ስነ ስርዓት እየተካሔደ ነው፡፡

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ዛሬ በኢንሴኖ ከተማ ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓት እየተካሔደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓቱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልል እና የዞን የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!