ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶሪያው ፕሬዚዳንት 900 ሺህ  ተፈናቃዮችን ለመመለስ ቃል ገቡ

By Tibebu Kebede

February 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ 900 ሺህ ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራው እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡

የሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ በመጨረሻው የአማጽያን ይዞ ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት እንደሚቀጥል ቃል የገቡ ሲሆን ጦርነቱ ባይጠናቀቅም ወደ ድል እየተቃረብን ነው ብለዋል፡፡

በሩሲያ መንግስት የሚደገፈው የሶሪያ መንስግስት በወሰደው እርምጃ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ ግዛት 900 ሺህ ሰዎች  ተፈናቅለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቀውሱ ምክንያት  ሰዎች በከፍተኛ ቅዝቃዜ ውጭ ላይ መኖር ግድ እንደሆነባቸው ይፋ ያደረገ ሲሆን÷ የስደተኞች ካምፖች በመሙላታቸው ከፍተኛ ቅዝቃዜ ባለው የአየር ንብረት ህፃናት ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አል አሳድ በቴሌቪዥን ቀርበው ባስተላለፉት መልዕክት በቅርቡ በተካሄደ ዘመቻ የአሌፖ ግዛትን ለተቆጣጠረው ጦራቸው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፡-አልጀዚራ