የሀገር ውስጥ ዜና

አገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ ከመገናኛ ብዙሃን እና ከባለሙያዎች ብዙ ይጠበቃል – ምሁራን

By Feven Bishaw

January 10, 2022

አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ ከመገናኛ ብዙሃን እና ከባለሞያዎች ብዙ እንደሚጠበቅ ምሁራን ገለጹ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር አደም ጫኔ እና የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጉዳይ ተመራማሪው በቀለ ሀብታሙ÷ መገናኛ ብዙሃን ሂደቶቹን ከወዲሁ እየተከታተሉ ዜጎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው አካሄዱም ሁሉን አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ መቻል አለባቸው ብለዋል።