Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጥሩ ቡድን ይዘን ለመቅረብና ማንነታችንን ለማሳየት ተዘጋጅተናል – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርዴ ጋር ከምታደርገው ጨዋታ ቀደም ብሎ ዛሬ የቡድኑን ዝግጅት እና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ፥ ከሶስት አፍሪካ ዋንጫዎች በኋላ ወደ መድረኩ በመመለስ ጥሩ ቡድን ይዘው ለመቅረብ እና ማንነታቸውን ለማሳየት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

ከስምንት ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ እንደመመለሳቸው አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ዘንድሮ ለሚተገበረው ቪኤአር ቴክኖሎጂ አዲስ ቢሆኑም ያን ያህል ልዩነት እንደማይፈጥር ተናግረዋል።

በዘንድሮው ውድድር ላይ ዝቅተኛ ግምት እንደተሰጣቸው ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ውበቱ፥ ” ሁሉም ሰው ለእኛ አነስተኛ ግምት ነው የሰጠን። የፊፋ ደረጃ ላይ ያለን ቦታ ዝቅተኛ ነው፤ ደረጃው ግን ያለንበትን ሁኔታ አመላካች ነው ለማለት ይከብዳል” ነው ያሉት በምላሻቸው።

“ሁላችንም እንደምናውቀው ተጋጣሚዎቻችን ጠንካሮች እና በጥሩ ተጫዋቾች የተዋቀሩ ናቸው፤ ሆኖም እኛም ለመፎካከር እና ያለንን ነገር ለማሳየት ተዘጋጅተናል” ብለዋል።

አምበሉ ጌታነህ ከበደ በበኩሉ፥ የነገውን ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ ለማከናወን እንደተዘጋጁ ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ነገ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የምድቧን የመጀመሪያ ጨዋታ ከኬፕ ቨርዴ ጋር ታደርጋለች፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version