ዓለምአቀፋዊ ዜና

በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 868 ደረሰ

By Tibebu Kebede

February 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1ሺህ 868 ደርሷል፡፡

በሀቤይ ግዛት ተጨማሪ የ93 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ በሌሎች አምስት የሀገሪቱ ክፍሎች ተጨማሪ ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ የጤና ኮሚሽን  አስታወቋል ፡፡

ይህ ዜና ይፋ የሆነው የውሃን ውቻንግ ሆስፒታል ዳይሬክተር ሊዙ ዙሚንግ  በኮሮኖ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ መሆኑን የሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል፡፡

መንግሥት በመላ ሀገሪቱ ተጨማሪ 1 ሺህ 886 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃተቸውን ያስታወቀ ሲሆን በርካታ የተጠቂዎች ቁጥርን የምትይዘው የሁቤይ ግዛት ሆናለች፡፡

አጠቃላይ በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 72 ሺህ 436 መድረሱ ይፋ ሆኗል።

እስከ ፈረንጆቹ የካቲት 11 ድረስ 1 ሺህ 716 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 5 ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ምንጭ፡-አልጀዚራ