Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፖምፒዮ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የሁለቱን አገሮች የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ።

በተጨማሪም ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Exit mobile version